Homeዜናና ወቅታዊዜናአሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ለመቀልበስ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ...

አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ለመቀልበስ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ አቀረበች

የአሜሪካ መንግሥት በሶሪያ ላይ የጣለውን ማእቀብ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሀገሪቱ ማቅረቡን የዘገበው ሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ስድስት ምንጮችን ዋቢ ያደረገው የዜና ወኪሉ፤ ሰነዱን ለሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አሰድ አሸባኒ ያቀረቡት የቀጣናው የአሜሪካ ባለስልጣናት መሆናቸውን አስነብቧል፡፡ ባለሥልጣናቱ ሰነዱን ያስረከቡት በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደ የሶሪያ ድጎማ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡

የዜና ተቋሙ ለዘገባ ዋቢ ካደረጋቸው መካከል ሁለት የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና በቀጣናው የሚሠሩ የሶሪያ ዲፕሎማት ይገኙበታል፡፡ እንደ ምንጮቹ ከሆነ በዩናይትድ ስቴትስ ከቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ሶሪያ የቀሩ የኬሚካል የጦር መሣሪያ ማከማቻዎች እንዲወድሙ ማድረግ እና ለፀረ-ሽብርተኝነት ትብብር ማድረግን የሚጠይቀው ተካቷል፡፡ ሌላኛው ጥያቄ የውጭ ሀገራት ተዋጊዎች በሶሪያ አስተዳደር መዋቅር ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ እንዳይቀመጡ ማረጋገጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

ሁለቱ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና የዋሽንግተን ምንጮች እንዳሉት ደግሞ፤ የትራምፕ አስተዳደር ከአስር ዓመት በፊት በሶሪያ ውስጥ የጠፋውን የአሜሪካ ጋዜጠኛ ኦስቲን ታይስን ለማግኘት የአሜሪካን ጥረቶችን ለማገዝ ሶሪያ የግንኙነት ሰው እንድትመድብ ተጠይቃለች። በቅድመ ሁኔታ ለተቀመጠው ዝርዝር አሜሪካ የምታነሳቸው ማዕቀቦች የትኞቹ እንደሆኑ አልተገለጸም፡፡

በቀድሞው የበሻር አል አሰድ አገዛዝ ወቅት ከአሜሪካ በተጨማሪ የአውሮፓ ኅብረትም በሶሪያ ላይ ማእቀብ እንደጣለ ይታወቃል፡፡ በአሕመድ አሸረእ የሚመራው አዲሱ የሀገሪቱ አስተዳደር፤ ማእቀቡ እንዲነሳ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular