Homeየቲቪ ፕሮግራሞችየቱርክ መስጂዶች የቤተሰብን ክብር እና ፍቅር በሚያጎሉ መልዕክቶች አሸብርቀዋል

የቱርክ መስጂዶች የቤተሰብን ክብር እና ፍቅር በሚያጎሉ መልዕክቶች አሸብርቀዋል

በረመዳን ወር የቱርክ መስጂዶች የቤተሰብን ፍቅር እና ክብር በሚያጎሉ መልዕክቶች አሸብረቀው ታይተዋል፡፡ መስጂዶቹ መልዕክቶቹን እንዲያጎሉ ያስተባብረው የሀገሪቱ የቤተሰብ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነው፡፡

ዴይሊ ሰባህ የተሰኘ ድረ ገጽ እንደዘገበው፤ መስጂዶቹ በሚናራ ላይ ከሰቀሏቸው መልዕክቶች መካከል “ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት ነው”፤ “ቤተሰብ የወደፊት ሕይወት”፤ “ቤተሰብ ሐብት ነው”፣ “ከእናንተ ውስጥ ከሁሉ በላጩ ለቤተሰቦቹ መልካም የሆነው ነው” እና “የምድር ገነት – ቤተሰብ” የሚሉት ይገኝበታል፡፡

የቤተሰብ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ማሂኑር ኦዝዴሚር፤ በማኅበራዊ ትስስር ላይ ባሠፈሩት መልዕክት፤ “ረመዳን የጥንት እሴቶቻችን የሚታደሱበት ጊዜ ነው። በተባረከው በዚህ ወር ለዘመናት የቆዩ እሴቶችን ኅብረተሰቡ እንደማዕዘን ድንጋይ ከሚቆጥራቸው የቤተሰብ መልዕክቶች ጋር አጣምረናል” ብለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular