Homeዜናና ወቅታዊዜናበአውሮፕላኑ ውስጥ የታየው ጭስ መነሻ የዘይት ቃጠሎ መሆኑን አየር መንገዱ ገለጸ

በአውሮፕላኑ ውስጥ የታየው ጭስ መነሻ የዘይት ቃጠሎ መሆኑን አየር መንገዱ ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐዋሳ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ አውሮፕላኑ ላይ ጭስ የታየው ውስጡ በሚገኝ ዘይት ሳቢያ መሆኑን በሥራ አስፈጻሚው በኩል አስታወቀ። አየር መንገዱ የተፈጠረው ጭስ “የተለመደ ነው” ብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የተፈጠረው ክስተት በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለው ዘይት ከመቃጠሉ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማብራሪያ የመጣው ሚያዝያ 29/2016 ከሐዋሳ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ አውሮፕላን ላይ ጭስ መታየቱ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡ ክስተቱን በዕለቱ ቀድሞ ይፋ ያደረገው አየር መንገዱ፣ አውሮፕላኑ በሰላም እንዳረፈ ገልጾ ነበር፡፡ አየር መንገዱ በመግለጫው ጭስ ታይቶበታል ያለው አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ET154 ነው፡፡

ከሐዋሳ የተነሳው የአየር መንገዱ ንብረት የሆነ አውሮፕላን፣ አዲስ አበባ ደርሦ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ላይ “ያለ ምንም እክል” በመቆም መንገደኞች “ደህንነታቸው እንደተጠበቀ” መውረዳቸውንም የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular