Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዓለም አቀፉ እስላማዊ የአየር ንብረት ጥምረት መሥራች አባል ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዓለም አቀፉ እስላማዊ የአየር ንብረት ጥምረት መሥራች አባል ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ31 ጉባዔ ጎን ለጎን በይፋ በተመሠረተው የዓለም አቀፉ እስላማዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ ጥምረት (GICFA) ውስጥ በመሥራች አባልነት መቀላቀሉን አስታውቋል።

ማዕከላዊ ባንኩ ባሠራጨው መረጃ እንዳመለከተው፣ ከወለድ ነጻ ባንክን ማስፋፋት የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ላልሆነላቸውና በቂ አገልግሎት ያልተሰጣቸውን ማኅበረሰቦች ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዐት ለማምጣት ስለሚረዳ፣ ጥምረቱ ከኢትዮጵያ የፋይናንስ አካታችነት አጀንዳ ጋር ይጣጣማል።

በተጨማሪም ጂ.አይ.ሲ.ኤፍ.ኤ እንደ ግሪን ቦንድ እና ሱኩክ ባሉ አዳዲስ የፋይናንስ ምርቶችና አገልግሎቶች አማካኝነት ሐብት ለማሰባሰብ አማራጭ መድረክ ይፈጥራል። እስላማዊ ፋይናንስን ከዋናው የአየር ንብረት ፋይናንስ ጋር ያስተሳስራል።

ከዚህም ባሻገር ጥምረቱ በአባል ተቋማት መካከል ለዕውቀት ሽግግር፣ ለአቅም ግንባታ እና ለልምድ ልውውጥ ጠቃሚ መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የቀጣናው የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት ማዕከል ለመሆን የያዘችውን ራዕይ ለማሳካት እንደ ተጨማሪ አቅም ነው።

ባንኩ ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የሚካሄደውን የኮፕ32 ጉባዔ የምታስተናግድ እንደመሆኗ መጠን፣ ይህንን ጥምረት በእስላማዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ እና በዘላቂ ልማት ዙሪያ የፖሊሲ ውይይቶችን ለመምራት እንዲሁም ጥምረቱን ከዕቅድ ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንደ አንድ ዋነኛ መድረክ ትጠቀምበታለች ብሏል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular