Homeዜናና ወቅታዊዜና“ገበያ እንዴት ዋለ?”

“ገበያ እንዴት ዋለ?”

“ገበያ እንዴት ዋለ?” ሚንበር ቲቪ እስላማዊ ፋይናንስ እና የሙስሊሙን ዓለም ኢኮኖሚ ከሀገር ቤት ኸበር ጋር በማጣመር የሚያቀርብበት ነው፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ “ገበያ እንዴት ዋለ?” ብለን አጣርተን የትም ያልሰማችሁትን መረጃ ለእናንተ ለክቡራን ተከታታዮችቻችን እናቀርባለን፡፡ የዛሬን እንሆ፦

1/ የእስላማዊ የጋራ ብድር የ5 በመቶ ዕድገት አሳየ

እ.አ.አ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና ገበያዎች የተመዘገበው የእስላማዊ የጋራ ብድር አቅርቦት ከዓመት ዓመት የ5 በመቶ ዕድገት በማሳየት 48.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን ፊች ሬቲንግስ አስታውቋል። ይህም አጠቃላይ ከተሰጠው የጋራ ብድር መጠን ከ28 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ የእስላማዊ ሲንዲኬትድ ፋይናንስ ብድሮች ጠቅላላ መጠን ደግሞ ከ221 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ማለፉ ተገልጿል።

2/ የማሌዥያው ቢፒፒ ሶላር 131.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ አረንጓዴ ሱኩክ ፕሮግራም አስመዘገበ

የማሌዥያው የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክቶች አምራች እና ኢንቨስተር ቢፒፒ ሶላር፤ 131.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የደቡብ ምሥራቅ እስያ መንግሥታት ማኅበር ሱኩክ ሙራባሃ ፕሮግራም በማሌዥያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ኮሚሽን “ሎጅ ኤንድ ላውንች” (Lodge and Launch) ማዕቀፍ አማካኝነት አስመዘግቧል። ኩባንያው ያስመዘገበው ሱኩክ ሙራባሃ በኢስላማዊ የሸሪዓ መርህ በሙራባሃ ውል የተዋቀረ፣ ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ የገንዘብ ምንጭ የሚሰበሰብበት እና የተሰበሰበው ገንዘብ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ለሚከናወኑ የተረጋገጡ የአካባቢ ጥበቃ እና የንጹህ ኃይል ፕሮጀክቶች ብቻ እንዲውል የተዘጋጀ የፋይናንስ ሰነድ ነው።

3/ ባንግላዴሽ ብሩናይ በእስላማዊ ባንክ ዘርፏ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ጥሪ አቀረበች

የባንግላዴሽ ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁማዩን ከቢር ጥሪውን ያቀረቡት በዚህ ሣምንት በተካሄደው የኮመንዌልዝ የሀገራት መሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሩናይ የፋይናንስ ሚኒስትር ዶ/ር አሚን ሊው ዓብዱላህ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።

4/ የአቡ ዳቢ ኮሜርሻል ባንክ በካዛክስታን የኢስላማዊ የባንክ አገልግሎት መስኮት ሊከፍት ነው

የአቡ ዳቢ ኮሜርሻል ባንክ (ADCB) በካዛክስታን የሚገኘውን ተቅጥላ የኢስላማዊ ባንክ ቅርንጫፍ አዲስ ወደተቋቋመው ኤዲሲቢ ካዛክስታን ለማዛወር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሀገሪቱ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ተቋም አስታውቋል። አዲሱ ተቋም በካዛክስታን ኢስላማዊ የባንክ አገልግሎት በመስኮት በኩል የፋይናንስ መፍትሔዎችን ለማቅረብ ነው።

5/ የኢነርጂ ዴቬሎፕመንት ኦማን  የሱኩክ ሰነዶች ሽያጭ እና ምዝገባ መክፈቱን አስታወቀ

የኦማኑ አነርጂ ዲቨሎፕመንት ኦማን ለ5 ዓመታት የሚቆይ የሱኩክ የፋይናንስ ሰነድ የመጀመሪያ ደረጃ ምዝገባ ለተቋማዊ ባለሐብቶች ክፍት ማድረጉን አስታውቋል። የሱኩክ ሽያጩ 50 ሚሊዮን የኦማን ሪያል ለመሰብሰብ አልሟል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ለተቋማዊ ባለሀብቶች የተከፈተ ሲሆን፣ ለግለሰብ ባለሐብቶች የተዘጋጀው ሁለተኛው ምዕራፍ ከኅዳር 9 እስከ 21 ይካሄዳል።

6/ ባንክ አልጀዚራ የሱኩክ ሰነዶች ሽያጭ ጀመረ

በሳዑዲ ዐረቢያ የሚገኘው ባንክ አልጀዚራ በ3 ቢሊዮን የሳዑዲ ሪያል የሱኩክ መርሃ ግብሩ ስር ደረጃ-2 ካፒታል የሚያድግበትን የሱኩክ ሰነዶች የግል ሽያጭ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

7/ ገልፍ ባንክ ሙሉ በሙሉ ወደ እስላማዊ ባንክ ለመቀየር ከኩዌት ማዕከላዊ ባንክን ፈቃድ አገኘ

ገርልፍ ባንክ አጠቃላይ የባንክ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ኢስላማዊ ባንክ ለመቀየር ከኩዌት ማዕከላዊ ባንክ ይፋዊ ፈቃድ አግኝቷል። ይህም ባንኩ ከመደበኛው የባንክ አሰራር ወደ ኢስላማዊ የባንክ አገልግሎት በሚያደርገው ሽግግር ውስጥ ትልቅ የህግ እና የቁጥጥር ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

ባንኩ ለኩዌት የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ቡርሳ ኩዌት በሰጠው መግለጫ ሙሉ መስፈርቱን በማሟላቱ የሽግግር ሂደቱን ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የመጨረሻ ፈቃድ አግኝቷል።

ይህን ተከትሎም ባንኩ የቀሩትን የሽግግር ሂደቶች ካጠናቀቀ በኋላ፣ ከመደበኛው ባንኮች መዝገብ ተሰርዞ በኢስላማዊ ባንኮች መዝገብ ውስጥ እንዲካተት ለኩዌት ማዕከላዊ ባንክ ማመልከቻ ያቀርባል ተብሏል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular