Homeዜናና ወቅታዊዜናሐማስ ከኻሊድ ሚሻል እና ኸሊል አል ሐያ አንዳቸውን መሪ አድርጎ ለመምረጥ በቀጣይ...

ሐማስ ከኻሊድ ሚሻል እና ኸሊል አል ሐያ አንዳቸውን መሪ አድርጎ ለመምረጥ በቀጣይ ሣምንት ስብሰባ ሊያካሄድ ነው

የፍልስጤሙ ሐማስ ከሁለት ዓመት በፊት የተገደሉትን የፖለቲካ ቢሮ መሪው የየሕያ ሲንዋርን ተተኪ ለመምረጥ በቀጣዩ ሣምንት ስብሰባ ሊያካሄድ ነው፡፡ በተተኪነት ታጭተው ድምጽ የሚሰጥላቸው ለቀድሞው የቡድኑ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኻሊድ ሚሻል እና ለቀድሞው ምክትል መሪ ኸሊል አል ሐያ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ ተመራጭ የሚሆነው ግለሰብ ከቀድሞዎቹ መሪዎች እስማኤል ሐኒያህ እና የሕያ ሲንዋር በኋላ የአመራርነት ሚና እየተወጣ የሚገኘውን የሽግግር ምክር ቤት ሥልጣን በመረከብ ቀጣዩ ምርጫ እስከሚደረግበት እ.አ.አ 2027 ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

በሐማስ የውስጥ ደንብ መሠረት፣ አንድ እጩ መሪነቱን ለማሸነፍ በቡድኑ አማካሪ አካል በሆነው በሹራ ምክር ቤቱ ውስጥ የ50 በመቶ ሲደመር አንድ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ሁለቱም እጩዎች ይህን የድምጽ መጠን ማግኘት ባለመቻላቸው አሸናፊውን ለመለየት ለሚቀጥለው ሣምንት የድጋሚ ምርጫ ተቀጥሯል፡፡

አልጀዚራ አንድ ምንጭን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በ2021 በተቀረጸው ማዕቀፍ መሠረት፣ ሁለቱ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎች የየግዛቱን ተወካይ ማካተት አለባቸው፡፡ ጋዛ ሐማስ ከተከፈለባቸው መልክዓ ምድራዊ ቀጣናዎች አንዱ ሲሆን፣ የቀሩት ሁለቱ የዌስት ባንክ እና የዲያፖራ ክልሎች ናቸው፡፡ የጋዛ ተወካይ የሆኑት አል ሐያ በድጋሚ ምርጫው መሪነቱን ማሽነፍ ካልቻሉ፣ በምክትል የፖለቲካ ቦታ ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለሐማስ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳረጋገጡት፤ በቀጣይ ሣምንት የሚካሄደው ምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን እንደ ጸጥታ ሁኔታው የሚወሰን ሆኖ፣ በሚቀጥለው ዓመት በሦስቱም ቀጣናዎች አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ በቡድኑ ቀጠሮ ተይዟል፡፡

የአሁኑ የምርጫ ማዕቀፍ የተቀረጸው በ2021 መከመርያ ላይ ከተካሄደው የውስጥ ጠቅላላ ምርጫ ነው፡፡ በወቅቱ ሐኒያህ የፖለቲካ ቢሮ የበላይ መሪ ሆነው ሲመረጡ፣ ሲንዋር ደግሞ ጋዛን እንዲመሩ በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡ ሚሻል ደግሞ በውጭ ሀገር የሚገኘውን የንቅናቄውን የዲያስፖራ ክንፍ እንዲመሩ ተመርጠው ነበር፡፡

እስራኤል በርካታ የሐማስ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራር እርከኖችን ዒላማ ያደረገችበትን ጦርነት ተከትሎ፣ ይህ ተቋማዊ መዋቅር ከዚህ ቀደም ታይቶ አይታወቅም የተባለ መስተጓጎል ገጥሞታል፡፡ በሐምሌ 2024 የፖሌኢካ መሪው እስማኤል ሐኒያህ በቴህራን የተገደሉ ሲሆን፣ ሲንዋርም እንዲሁ በ2024 በራፋህ ሲገደሉ፣ ቡድኑ የጦርነት ጊዜ አስተዳደርን እና ድርድሮችን እንዲመራ አምስት አባላት ያሉት ጊዜያዊ የአመራር ምክር ቤት አቋቁሟል፡፡ ይህ የሽግግር ኮሚቴ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኳታር በሚኖሩት ሙሐመድ ዳርዊሽ እየተመራ ይገኛል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular