Homeዜናና ወቅታዊዜናአዋሽ ባንክ በዓመቱ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ በእጥፍ ማደጉን...

አዋሽ ባንክ በዓመቱ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ በእጥፍ ማደጉን አስታወቀ

አዋሽ ባንክ በ2017 ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ በእጥፍ ማደጉን ያስታወቀው የሒሳብ ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሺፈራው፤ በሒሳብ ዓመቱ ውጤታማ አፈጻጸም ካስመዘገበባቸው ክንውኖች መካከል ከወለድ ነጻ አገልግሎት እንደሚገኝበት ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ “በ2017 የሒሳብ ዓመት ትልቅ ሥራ ሰርተንበታል ብለን የምንገልጸው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አፈጻጸም ነው” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ፀሐይ ከሆነ፤ ባንኩ በ2016 የሒሳብ ዓመት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ማሰባሰብ የተቻለው ተቀማጭ ገንዘብ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ በ2017 የሒሳብ ዓመት ግን ተቀማጭ ገንዘብ 37 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱንም አስረድተዋል፡፡ ይህ አፈጻጸም ከመቶ ፐርሰንት በላይ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ ምንዛሬ ግኝት አንፃርም ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በተለይ ላኪዎችን በሰፊው በማገዝና የሚፈልጉን የሥራ ማስኬጃ በተገቢው መንገድ ማቅረብ በመቻሉ፣ በሒሳብ ዓመቱ ከተገኘው የውጭ ምንዛሬ አንድ ቢሊዮን ዶላር የተመዘገበው ከዚሁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በላኪዎች አማካኝነት ከተገኘው አንድ ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ገቢ የተገኘው ደግሞ ከቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ ከሐዋላ እና ከሌሎች የውጭ ምንዛሪ መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular