Homeዜናና ወቅታዊዜናየአል ነጃሺ መስጅድ ጥገና በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል ተባለ

የአል ነጃሺ መስጅድ ጥገና በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል ተባለ

የታሪካዊው አል ነጃሺ መስጅድ ጥገና፣ በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል ያለው የቱሪዝም ሚኒስቴር ነው፡፡ ለመስጅዱ ጥገና የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ደርጋል የተባለው የቱርክ መንግሥት ነው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 15/2016 እንዳስታወቀው ከሆነ፣ መስጂዱን በተመለከተ ከቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር ተከታታይ ውይይት ተካሄዷል፡፡ በዚህም የቱርክ መንግሥት “አስፈላጊውን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ” ስምምነት ላይ መድረሱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡  

ሚኒስቴሩ አያይዞም ለመስጅዱ “ደረጃውን የጠበቀ የጥገና ሥራ” ለማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጧል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስቴር ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ለመሥራት ቅድመ ዝጅት መጠናቀቁን ቢገልጽም ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጠም፡፡

ጥገና ሊከናወንለት ነው የተባለው አል ነጃሺ መስጅድ ከትግራይ ክልል ዋና መቀመጫ መቐለ ከተማ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ መስጅዱ በ2013 አጋማሽ በአካባቢው በነበረው ጦርነት ጥቃት ያስተናገደ ቢሆንም ጥቃቱ በማን እንደተሰነዘረ እስካሁን ድረስ የታወቀ ነገር የለም፡፡

የአል ነጃሺ መስጅድ ከአምስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ በቱርክ መንግሥት ድጋፍ ጥገና የተደረገለት ነው፡፡

አል ነጃሺ መስጅድ በ4 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ዋነኛ የጸሎት ቦታ እና ሁለት የቀብር ሥፍራ የያዘ ነው፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular