እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeሚንበር ሼልፍማሰብና መለወጥ

ማሰብና መለወጥ

ማሰብና መለወጥ

በርካታ ጌዜያት ስለመለወጥ አስበናል፡፡ በርካታ የማያዳግም የሚመስሉ ውሳኔዎችን ወስነን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተመሳሳይ ሁኔታን ሁኔታን በተደጋጋሚነት አስተናግደናል፡፡ ይህ የሆነው ከውስጣችን ለመነጨው የመለወጥ ጥያቄ መልስ ስለመስጠታችን አይደለም፡፡ ነገሩ የሰጠነው ምላሽ ካለመውደዳችን ነው፡፡ ምላሹ የሚሻውን መስዋዕትነት ስላልከፈልን ነው፡፡

መለወጥ መፈለግ ብሎም ጎዳናውን መጀመር ወኔን ይጠይቃል፡፤ ኃላፊነት መውሰድን ይፈልጋል፡፡ ካለንበትና ከለመድነው ሁኔታ ውስጥ ፈልቅቆ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ነበር ታላቁ ነብይ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከሚወዱት ሀገራቸው መካ ብሎም ከቅርብ ዘመዶቻቸው ተገንጥለው የዘመን አቆጣጠር ጅማሬ የሆነውን ሂጅራን ያስከሰቱት፡፡ ለውጥ ሲጀምር ያሉበትን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡ በአዳዲስ ሁኔታዎች መከበብን ያስከትላል፡፡ አዳዲስ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ይጠይቃል፡፡

የቅርብ ዘመዶች የነበሩት የቁረይሽ ጎሳ አባላት ታላቅ መከራን እንዲያስተናግድ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ቢሆንም ግን መልእክተኛው ወደፊት ተጉዘዋል፡፡ የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመዋል፡፡ ማህበራዊ ሆነ ግላዊ ለውጦች ተመሳሳይ መስፈርት ያስቀምጣሉ፡፡ ያሉበትን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ወኔ ጠያቂ ውሳኔዎችን መወሰን፡፡ ሁሉም ወደ ለውጥ የሚደረግን ጉዞ ያጅባሉ፡፡ የእስልምናን እሴቶች መርሆች እንደሚያከብር ሰብአዊ ፍጡር ቆራጥነትና ቀጣይነት ዋነኞቹ መርሆች መሆናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ እስልምና የአንድ ጌዜ ተግባር አይደለም፡፡ እራስን ለህይወት ዘመን ቀጣይነት ላለው እሴቶችን፣ መርሆችንና ሕጎችን የማክበር ሁኔታ አሳልፎ መስጠት እንጂ፡፡

ለውጥን የማምጣት እንቅስቃሴ ከማንነታችን ጋር አብሮ የተወለደ አቅም ሳይሆን በመማር ሂደት ውስጥ የሚቸሩት ክህሎት ነው፡፡

በተለይ ደግሞ እስልምና ላይ የሚዳረጉ ጥቃቶች በበዛበት ሁኔታ ውስጥ ቀለል ካለ የመለወጥ ተነሳሽነት ተሸግረን ከፍ ላለ ደረጃ ብሎም ለሁለንተናዊ ምጥቀት ልንተጋ ይገባል፡፡ ይህን ልናደርግ የሚያደርገን የአላህ የምድር ምትኮች የመሆን ኃላፊነት መሸከማችን ደግሞ ሊታወስ ይገባል፡፡

በላቀና ከፍ ላለ የማንነት ደረጃ ልናስስ ይገባናል፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ የምናስመዘግበው የስኬት ጉዞ ለሰው ልጆች ብርኃን ሊሆን ይፈለጋል፡፡

“ለሁሉም እርሱ (በስግደት ፊቱን) የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው፡፡ ወደ መልካም ሥራዎችም ተሽቀዳደሙ፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑ አላህ እናንተን የተሰበሰባችሁ ኾናችሁ ያመጣችኋል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡” (አል በቀራ፤ 148)

“አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡” (አል ረእድ፤ 11)

በነዚህ አናቅፅ ውስጥ የለውጥ መርሆች አንዱ የሆነውን ንፉግነትን እንረዳለን፡፡ ለለውጥ ክፍት መሆንና ፍላጎት ማሳደር ከታላላቅ የለውጥ መርሆች አንደኛው መሆኑንም ጭምር እናውቃለን፡፡

አለም አቀፍ ሁኔታ በርካታ ልብን የሚያደሙ ክስተቶችን እያሳየን ይገኛል፡፡ እንደ ሙስሊም ለተጎዳውና ለተበደለው ሠብአዊ ፍጡር የመድረስ መነሳሳት መኖሩ አይቀሬ ነው፡፡ ነገር ግን ለአለም እራሳችንን ሰላም፣ ፍትህ፣ መልካምነትና መረዳዳት በግላችን ህይወት ውጥ ማጣጣም መጀመር በራሱ የነዚህን መልካም እሴቶች በማህበረሰባችን ውስጥ የማምጣትን አቅም ያበስራሉ፡፡

ለውጥን የማምጣት እንቅስቃሴ ከማንነታችን ጋር አብሮ የተወለደ አቅም ሳይሆን በመማር ሂደት ውስጥ የሚቸሩት ክህሎት ነው፡፡ በእርግጥ ጉዳዩ የመለወጥ አቅምንና ነፃነትን ወደ ተግባር የመቀየርና ያለመቀየር ብቻ ይሆናል፡፡

ለውጥ የሚፈልጋቸው መርሆች

የለውጥ ሂደት አራት መሰረታዊ መርሆች እንድናከብር ይጠይቃል፡፡

1. የለውጥ ምንጭ አላህ መሆኑን
2. የመለወጥ ነፃነት
3. ቆራጥ ትግል
4. የጋራ ጥረት

1. የለውጥ ምንጭ አላህ መሆኑን ማወቅ ስንል እያንዳንዱ ሂደታችን በርሱ ቁጥጥርና ስልጣን ስር መሆኑን መመስከር ማለት ነው፡፡ የኛ ችሎታና አቅምና ታግሎ የማሸነፍ ደረጃው ከርሱ ስልጣን አቅምና ዘዴ ብሎም እዝነት ጋር ሲነፃፀር እዚህ ግባ የማይባል ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ዘዴ አልባ መሆንን መረዳት ነው፡፡

2. የመለወጥ ነፃነት፦ ይህ መርህ ነፃነት የሚሰጠን ነገር ሳይሆን እኛ ስንፈቅድ የምናነሳው ነገር መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
“አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡”
(አል ረእድ፤ 11)
በዚህ አንቀፅ ውጥ ሁለቱንም መርሆች እንመለከታለን፡፡ የርሱን የመለወጥ ስልጣንና የሰውን ልጅ መለወጥ የመፍቀድ ነፃነት፡፡ ስለዚህ የመለወጥ ነፃነት መኖሩን መረዳት ዋነኛ መርህ ይሆናል፡፡

3. ቆራጥ ትግል በባህሪው እውነተኛና ትክክለኛ የለውጥ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ መንገዱ መራራ ነው፡፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ክስተቶች መንገዱ ላይ በርክተው ይገኛሉ፡፡ እኔ አልረባም፣ ዋጋ የለኝም፣ አሁንስ ሰለቸኝ፣ በቃ ለዚሁ ነው የተፈጠርኩት እና የመሳሰሉትን የምንልባቸው ቦታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ግን አሁንም ህይወት ሲቀጥል ትግልም ይቀጥላል፡፡ ሆድ መባስ፣ በራስ መናደድና በቀቢሰ ተስፋነት ያምናሉ፡፡ ቢሆንም ግን ወደ ለውጥ የሚደረግ ጉዞ አይቆምም፡፡ ሁኔታው እጅግ የገዘፈና ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳን ከምር የሚስበን ሀይል ከርሱ በላይ ነው፡፡

4. የጋራ ጥረት የጋራ ጥረት ሲኖር ግለሰባዊ ለውጦች ፈጣንና ስኬታማ ይሆናሉ፡፡ ይህ በሂጅራው ወቅት ተገኝቷል፡፡ ነብዩና ባልደረባቸው አቡበከር ለጉዞ ተነስተዋል፡፡ አስማ መቀነቷን አስራ ስንቅ ታመላልሳለች፤ አብዱራህማን ዜናዎችን ይከታተላል፤ ያደርሳል፡፡ ሌላኛው ባልደረባ መጓጓዣዎችን ያሰናዳል፡፡ በዚህ የጋራ ጥረት ውስጥ ሂጅራ በስኬት ተፈፀመ፡፡ ካለፈ ማንነት ውስጥ ተሰዶ መውጣትና ወደ አዲስ ማንነት መሸጋገርም ይህን እውነታ እና መርህ በሚገባ ይሻል፡፡
ስንደክም የሚያጠናክረን፣ አቅጣጫን የሚጠቁመን፣ መነሳሳታችን ሲሰማ የሚቆሰቁሰን የቅርብ ወንድምና እህት ያስፈልጋል፡፡

RELATED ARTICLES

ሚንበር ሼልፍ

የ ካሊድ መንገድ

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular