Homeዜናና ወቅታዊዜናዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክን ሙሉ በሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ሥምምነት ሊገዛ ነው

ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክን ሙሉ በሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ሥምምነት ሊገዛ ነው

ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ የተሰኘውን ባንክ ሙሉ ለሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ስምምነት ለመግዛት ተሥማምቷል፡፡ ግብይቱ ያለ ጥሬ ገንዘብ በአክስዮን ልውውጥ ብቻ የሚፈጸም ነው፡፡ ሥምምነቱ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ 100 በመቶ የኤሚሬትስ ኢስላሚክን ካፒታል ለመውሰድ በምትኩ ለኤሚሬትስ ኤን.ዲ.ቢ አዲስ መደበኛ አክስዮኖችን መስጠትን ያካትታል፡፡ ይህ ሥምምነት በሐብት መጠን በዓለም ሁለተኛውን ትልቅ በአክሲዮን የተመዘገበ እስላማዊ ባንክን ይፈጥራል ተብሏል፡፡

ሁለቱ ባንኮች በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሥምምነቱ ሲጠናቀቅ ኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ በዱባይ ኢስላሚክ ውስጥ ትልቅ ባለድርሻ ይሆናል፡፡ ሆኖም ባንኮች የግብይቱን አጠቃላይ ዋጋ፣ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የሚያወጣውን የአክሲዮን የአክሲዮን ብዛት ወይም የኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ የሚኖረውን የድርሻ መጠን ይፋ አላደረጉም፡፡

ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፤ አበዳሪዎች የአክስዮን ግዥ ሥምምነቱን ከመፈራረማቸው በፊት የሁለቱም ባንኮች የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥምምነቱን አጽድቀዋል፡፡ ነገር ግን ሥምምነቱ አሁንም የባለአክስዮኖችን ይሁንታ እንዲሁም ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ፣ ከካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ፈቃድ ይፈልጋል፡፡ ባንኮቹ ሥምምነቱ የሚጠናቀቅበትን ቀን አልገለጹም፡፡

እስከ መስከረም ድረስ ባለውና ኦዲት ባልተደረገ የፋይናንስ መረጃ መሠረት፣ አበዳሪዎቹ ከተጣመረ ሐብታቸው ወደ 159 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እንደሚሆን ገምተዋል፡፡ ይህ አኃዝ ከግብይቱ በኋላ የሚደረጉ የሒሳብ ማስተካከያዎችን የማያካትት ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውም የባንኮቹን ግምት የሚያንጸባርቅ ነው፡፡

ይህ ሥምምነት ዱባይ ኢስላሚክ ቀደም ሲል “ኑር ባንክ”ን በመግዛት በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የእስልምና ባንክ እንቅስቃሴውን ካሰፋ በኋላ የተደረገ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1975 የተመሠረተውና በዱባይ የፋይናንስ ገበያ የተመዘገበው ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ በፓኪስታን እና በኬንያ ቅርንጫፍ ባንኮች ያሉት ሲሆን፣ በኢንዶኔዥያ እና በቱርክ ደግሞ በእስልምና እና በዲጂታል ባንክ ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቶች አሉት፡፡

በዚህ ጥምረት ውስጥ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የትላልቅ ኩባንያዎች የባንክ አገለግሎት አቅሙን ይዞ የሚመጣ ሲሆን፣ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ ደግሞ የተደራጀ የግለሰብ/ችርችሮ የባንክ አገለግሎትና የተቀማጭ ገንዘብ መሠረትን ይጨምራል፡፡ እ.አ.አ በ2004 የተመሠረተው ኤሚሬትስ ኢስላሚክ በመላው የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች 36 ቅርንጫፎች አሉት፡፡ ለግለሰቦችና ለንግድ ተቋማት ከሸሪዓ ሕግ ጋር የተጣጣመ የፋይናንስ፣ የቁጠባ እና የሌሎች የባንክ አገለግሎቶች ይሰጣል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular