የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዝቅተኛ የደሞዝ እርከንን በተመለከተ መንግሥታቸው ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 17/2019 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራርያ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄና ማብራሪያ ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ “አሁንም ተጨማሪ ጥናቶች እያጠናን ነው፤ በተለይ “ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል”ን በሚመለከት የመንግሥቱም የግሉም ሠራተኛ እንዴት አድርገን ማስተካከል እንዳለብን፤ ወደ ሕግ ማምጣት እንዳለብን ጥናት እየተጠና ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አክለውም የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ችግር ሆኖ መቀጠሉን ጠቁመው፤ በማሻሻያው ምክንያት የሚያጋጥሙ ውስን የኑሮ ጫናዎችን ለመቅረፍና የዜጎችን ጫና ለማቃለል የተለያዩ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል። (ሚንበር ቲቪ)












