Homeዜናና ወቅታዊዜናአምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በጋዛ ሆነ ብላ የልደት መጠን እንዲቀንስ አድርጋለች በሚል የዓለም...

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በጋዛ ሆነ ብላ የልደት መጠን እንዲቀንስ አድርጋለች በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት ምርመራ እንዲያካሂድ ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ ልደትን የሚገቱ ወይም የሚከላከሉ እርምጃዎችን ወስዳለች በማለት፤ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) ጉዳዩን እንደ “የዘር ማጥፋት ድርጊት” አድርጎ እንዲመረምረው ጠይቋል።

አምነስቲ ጥያቄውን ያቀረበው ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 16፤ 2019 ‘አለም አቀፍ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ማስወገድ’ ቀንን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ነው፡፡ በዚህ ሪፖርት ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ባለሥልጣናት የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲመረምር ጥያቄውን አቅርቧል።

የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አግነስ ካላማር ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እስራኤላውያን ባለሥልጣናት የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ካላማር እንዳሉት ከጥቅምት 2016 ጀምሮ የተካሄደው ጦርነት በጋዛ ሴቶች አካላዊ፣ አእምሯዊና ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ ጉዳት አስከትሏል።

አክለውም እስከ 2019 ድረስ “የእስራኤል ድርጊቶች የመካንነት ሕክምና እንዳይገኝ፣ ለእርግዝና ችግሮች፣ ለፅንስ ማቋረጥና የሞተ ልጅ እንዲወልዱ አስተዋጽኦ አድርገዋል” ብለዋል።

እንደ ፍራንስ 24 ዘገባ ከሆነ ሪፖርቱ ነፍሰጡር እናቶችና ልጃገረዶች የወሊድ እንክብካቤ እና የሕክምና ርዳታ ፍለጋ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በደረሱ ጥቃቶች መገደላቸውን፣ እንዲሁም የማደንዘዣ መድኃኒቶችና በወሊድ ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ ደም መፍሰስን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶች እጥረት መኖሩን ሰንዷል።

በጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ መሠረት፣ እ.አ.አ በ2018 መጀመርያ አካባቢ የተመዘገበው በሕይወት ያሉ ሕፃናት ልደት ቁጥር ከ2015 ጋር ሲነጻጸር በግምት በ41 በመቶ ቀንሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በ2019 መጀመርያ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የወሊድ ቁጥር መቀነሱን መዝግቧል። አምነስቲ በሺዎች የሚቆጠሩ የተከማቸ ሽል፣ የወንድ ዘር እና እንቁላሎች መውደማቸውንም አመልክቷል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular