የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚገኙበት በመጪው ሐሙስ ኅዳር 17/2019 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 15፤ 2019 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2019 የመንግሥት እቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱ ሐሙስ ኅዳር 17፤ 2019 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው ላይ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ሚንበር ቲቪ)












