Homeዜናና ወቅታዊዜናወዶ ዘማች በጉራጌ ዞን ያስገነባውን ትምህርት ቤት ለማኅበረሰቡ አስረከበ

ወዶ ዘማች በጉራጌ ዞን ያስገነባውን ትምህርት ቤት ለማኅበረሰቡ አስረከበ

በወጣቶች ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው ​ወዶ ዘማች፣ ከኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናይዜሽን ባገኘው ድጋፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አረቅጥ ከተማ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባውን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቆ ለማኅበረሰቡ ማስረከቡን ለሚንበር ቲቪ በላከው መረጃ አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ወዶ ዘማች ኩኑዝ ኢኒስቲትዩት የላቀ አስተዋጽኦ ማበረከቱን በመግለጽ ኢኒስቲትዩቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል። ድርጅቱ በአካባቢው የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና የመማሪያ ክፍሎች እጥረትን ለመቅረፍ ካስገነባው ትምህርት ቤት በተጨማሪ፣ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር የሚውል 100 ሺሕ ብር ድጋፍ ማድረጉን የወዶ ዘማች አስተባባሪ አቶ ዓሊ አሚን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ገልጸዋል።

​ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገት መሠረት መሆኑን የገለጹት አስተባባሪው፣ ወዶ ዘማች በትምህርት ልማት ዘርፍ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጥቆማ ሰጥተዋል።

የአረቅጥ ከተማ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ተውፊቅ ቅባቱ በበኩላቸው፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት ጉልሕ ሚና ለተጫወቱ ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular