ማሰብና መለወጥ
ማሰብና መለወጥ በርካታ ጌዜያት ስለመለወጥ አስበናል፡፡ በርካታ የማያዳግም የሚመስሉ ውሳኔዎችን ወስነን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተመሳሳይ ሁኔታን ሁኔታን በተደጋጋሚነት አስተናግደናል፡፡ ይህ የሆነው ከውስጣችን ለመነጨው የመለወጥ ጥያቄ መልስ ስለመስጠታችን አይደለም፡፡ ነገሩ የሰጠነው ምላሽ ካለመውደዳችን ነው፡፡ ምላሹ የሚሻውን መስዋዕትነት ስላልከፈልን ነው፡፡ መለወጥ መፈለግ ብሎም ጎዳናውን መጀመር ወኔን ይጠይቃል፡፤ ኃላፊነት መውሰድን ይፈልጋል፡፡ ካለንበትና ከለመድነው ሁኔታ ውስጥ ፈልቅቆ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ …