ሚንበር መጣጥፍ

ከቀልባችን ጋር የሚደረግ ትግል። ከነፍሲያችን፣ ከፍላጎታችን፣ ከራሳችን ጋር…የሚደረገው ትግል ነው ታላቁ ጂሃድ።

 

ኢብን ሙፍሊህ በአል-አዳብ አሽ-ሻሪእያ-131 እንዳስተላለፉት ዑመር ኢብን አቡዱልአዚዝ ከጂሃድ ሁሉ የተወደደው ጂሃድ ከፍላጎት ጋር የሚደረገው ትግል ነው ብለዋል።

 

أَفْضَلُ الْجِهَادِ جِهَادُ الْهَوَى

 

ከቅዱስ ቁርዓን፣ ከሐዲስ…በተጨማሪ ከላይ ለምሣሌ እንደጠቀስነው በርካታ ታላላቅ ሙስሊም ምሁራን ስለታላቁ ጂሃድ፤ ከነፍሲያ ጋር ስለሚደረገው ትግል፤ ራስን ስለማሸነፍ፤ ልብን ስለማጽዳት፤ ውስጥን ስለማጥራት…በሰፊው ጽፈዋል። ኢብን አል-ጃውዚ፣ ኢብን አል-ቃይም፣ አቡ ሐሚድ አል-ጋዛሊ…ወዘተ ሙስሊም ምሁራን ስለ “ታላቁ ጂሃድ” በአትኩሮት ጽፈዋል። በሌሎች መስኮችና ዘርፎች ድል ለመቀዳጀት በቅድሚያ ራስን ማሸነፍ ወሳኝ እንደሆነ በአጽንኦት አስተምረዋል።

 

🖋ከኢስልምና ሃይማኖትና ከሙስሊም ምሁራን ሌላ የሌላ እምነት ሊቃውንት፣ እውቅ የሳይንስ ሰዎችና ፈላስፎች…ወዘተ እንዲሁ ራስን ስለማሸነፍ በተደጋጋሚ ይወተውታሉ።

 

የቡድሂዝም እምነት መሥራች ተብሎ የሚታወቀው ቡዳሃ  ራስን ስለማሸነፍ እንዲህ ብሏል።

 

“ራስን ማሸነፍ 1000 ጦርነት ከማሸነፍ ይበልጣል።”

 

ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ ፕላቶ በበኩሉ እንዲህ ሲል ተናግሯል።

 

“የመጀመሪያና ታላቁ ድል ራስን ማሸነፍ ነው።”

 

አርስቶትል ለጥቆ እንዲህ ይላል።

 

“እኔ ጀግና ብዬ የምጠራው ራሱን ያሸነፈን ሰው ነው።”

 

ሬኒ ዴካርት እንዲሁ እንዲህ ሲል ያሳስባል።

 

“ዓለምን ከማሸነፍ ይልቅ ራስህን አሸንፍ።”

 

“Think and Grow” በሚል ዝነኛ መጽሐፉ የምናውቀው ናፖሊዮን ሂል እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል።

 

“ራስህን ማሸነፍ ካልቻልክ በራስህ ትሸነፋለህ።”

.

.

.

ወዘተ

 

 

ነጃሺ ከድር ሻሞ

 

ዛሬም ወደትልቅ ሰው ደጆች ዘለቅን ። በብርሓን ወደተለሰኑት ። ወለላቸው በእውነት ሰሌን ወደተነጠፈ
ው ። ወጋቸው የመንፈስን ዝለት ወደሚረታው ። ታሪክ ስማቸውን ገላው ላይ ለመነቀስ ወደሚሻማው ። ወደትልቆቹ ። ወደጉምቱዎቹ ። ወደግዘፎቹ ። የግርማ ኩታ ወደለበሱቱ ። ወደጎራቸው የደከመ መንፈ
ሳችንን በስማቸው ምርኩዝ እየገደፍን እንቃናለን ። ስራቸው እንደትጥቅ ፣ ገድላቸውን እንደስንቅ ይዘን ነፍስ ወደሚያገነግን ኣውዳቸው እንራመዳለን ። ዳገት ቢኾንም ። ቁልቁለት ቢኾንም ። የሀር ንጣፍ ቢኾንም ። ያሻውን ቢኾንም ። ወዳሉበት እንኼዳለን ። ባንደርስም ዙርያውን እንጎዳጎዳለን ። ለሰጡን ለኾኑልን ላረጉልን የምንሸልመው ገለታ ነው ። ለሰጡን የምንሰጠው ለኾኑልን የምንኾነው ጥሪት የለን
ም ። የሰሩትን ማውጋትም ለኛ የማንከስርበት ንግዳችን ነው ። የማይበርድ ወረታችን ነው ። እንደሻማ ቀልጠዋልንና ገድላቸውን ለመዘከር ወገቤን የምንልበት የሞራል ጭብጥ የለንም ። ልባቸው ጌታን በማ
ስታወስ ኣቅላቸው የሱን ጉዳይ ለመረዳት ተጠምደዋልና ዋጋቸው የሁለት ዓለም ነው ። ትድረታቸው ደግ
ሞ ሁለት ቤት ። ከኣንደበታቸው በሚፈልቅ ቃል የዛሬ እና የነገ ጎጇቸውን የብርሓን ጡብ እየረበረቡ ያበጃሉ ። ይብላን ለእኛ ! እነሱማ የትውልድን የእዳ ሸክም ከጫንቃው ላይ ለማርገፍ በኣንድ ገላቸው የሺህ ሰው ላብ ፈልቋቸዋል ። እነሱማ ለእውቀት እና ለእውነት የዓለም ጠርዛ ጠርዝ እና ማዕዘናትን ማስነዋል ። ወርደዋል ወጥተዋል ። እነሱማ ስማቸው በዘመን እና በትውልድ የበቀለውን የስንፍና ቆፈን የሚያስከነዳ ስራቸው በቀን መግፋት ወለም የማይለው ነው ። ይብላኝ ለእኛ እንጂ ! በዘመን ፊት መል
ካችን ላልየ እንኳን ለሌላው ለገዛ እራሳችን የምናውሰው የብርታት ስንቅ የሌለን ! በመጣንበት የእጣ እግር ሾልከን ለምንወጣ ፣ የእድሜ ኪሳችን ቢበረበር ከባዶ ውጪ ላይደለ ! ይብላን ለእኛ ! የእነሱ ሕል ውናማ ተፈጠረ እና ሞተ በሚባል ተረክ ብቻ ኣይደመደም ። ህይወታቸውም ሞታቸውም የነፍስ ማር እና ወተት የሚፈልቅበት የኒዕማ ቀበሌ ነው ። ሲፈጥራቸው በእንዲህ ተሹመዋልና ። ከጌታ በማይሻር ልቅና ስር ለማርገድ ፣ ለክብሩ ከፍ ዝቅ ለማለት ተመርጠዋልና ። ልባቸው በዚክር ገላቸው በኣምልኮ ክሮች ተዘምዝሞ ፣ በኑር ሓረግ ተለጉሟልና ። ንግግራቸውም ዝምታቸውም ለጌታ ግርማ ተፈቅዷልና በቅርብ ኣዳሪ ኣለም ለደመቀ ስማቸው ኣይፍነከነኩም ። ነፍሳቸው ዘላለማዊውን የክብረት ወለል ሳይረ
ግጡ ኣያርፉም ። ቀን ሌቱን በብዕር ስለት የብራና መስክ እየቆፈሩ ፣ ኣይናቸው ከድርሳን ገበታ ላይ የፊደል ጥሬ እየለቀመች ይመሻል ይነጋል ። እንደሁሌው ባልጠና ክሂላችን ከምንመላለስበት የሒወት ቀበሌያቸው ዛሬም ኣንድ ዋርካ ለመጠጋት ተመኘን ። ተመኝተን ተጠጋን ። ግብጽ ዘለቅን ። ባህሩ ወደ
ፈለቁበት ። እነኾ የነፍስ ግዘፉ የከበደ ፣ የመንፈስ ግርማው የተሸለመ . . የትልቅ ሰው ብሩህ ወግ እነኾ ኸበር ።
በ1926 እ.ኣ ከእጅግ ደሃ ገበሬ ቤተሰብ ተወለዱ ። የህይወት ገጽ በድህነት እና ሌላም ሸክም ፊቱን ማወየብ የጀመረው በጣም በጧት ነበር ። በሁለት ኣመታቸው የቲም ኾኑ ። የየቲምነት ቀጣዩ የህይወት ጭብጥ ያረፈው ኣጎታቸው እጅ ላይ ነበር ። ብዙም ሳይሰነብት የዛ ህጻን ልጅ የብርሓን መንገድ ታየ ። ወደኣለም ይዞ የዘለቀው ራዕይ ገና የእድሜው ኣሓዝ ኣስር ሳይጠጋ ይገለጥ ያዘ ። በዘጠኝ ኣመቱ ታላቁን የጌታ ቃል በልቡ ኣሳደረ ። ሓፊዝ ኾነ ። ገና በማልዶ ህይወትን በውል ሳይተዋወቅ በመለኮታዊ ጎራ መቃናት ገራው ። ወዲያው የኢልም ፋናው የማይገታ የማይረታ እንደኾነ ቁርጥ እየኾነ መጣ ። ወዲያው በኣንድ የኢስላማዊ እውቀት እና ጥናት ማዕከል ተላከ ። ያ ፈኑ በእውቀት መስክ ተፈትቶ የተለቀቀው ታዳጊ ፈተናው ድህነቱ የቲምነቱ ሌላው ሌላው ሁሉ የሒወት ቁምስቅል ከጀንበር እሱነቱ እፍኝ የብርሓን ዘር ኣላጎደለም ። በፈተና ሸብረክ ኣላለም ። ያ ሰው ታላቁ ሸይኽ ዩሱፍ ኣብዱላህ ኣል ቀርዷዊ ይባላሉ ። ገና በልጅነት የተተከለው የብርሓን ካስማ ዛሬ የማይነቀንቁት ስም ኾኗል ። ይኼ ስም በኹለንተናዊ ኣበርክቶ በርካቶች ወደመዛል ቀበሌ ሲጠጉ የሚደገፉት ዋርካ ነው ። የያኔው ታዳጊ በታላላቆቹ ስብዕናዎች የጸጋ እና የእውቀት እድያ ተነሽጧል ። ከነኚህ መሓል ታላቁ ሸይኽ ሓሰን ኣህመድ ኣብዱልረህማን ሙሓመድ ኣልበና እና ሸይኽ ሙሓመድ ኣል ጟዛሊን እንጠቅሳለን ። ታላቁ ሸይኽ ሓሰን ኣልበና ለበርካታ የሓቅ ፈለግ ማሳኞች መንቂያ ታላቅ ስብዕና ናቸው ። ለዚህም የመርህ እና የኣስተሳሰብ ኩራዛቸው በጨለማ ከመደናበር ነጻ ያወጧቸው ስብዕናዎች እንደምሳሌ ይኾናሉ ። ከነዚህ መሓል የዛሬው ሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ሲኾኑ ታላቁ የሰው ልጅ የእኩልነት እና ነጻነት ተጋዳይ ማልኮም ኤክስም ተደምሮ ይጠራል ። ሸይኽ ሓሰን ኣል በና ይኼንን ያህል የስብዕና ተምሳሌትነት ዘውድ የጫኑት በዱንያ ላይ ብዙ ሰንብተው ኣይደለም ። የእድሜያቸው እና የተዉት ቁምነገር በኣንድ የኣሓዝ ሚዛን ቢሰፈር ኣይለካካም ። ሸይኽ ሓሰን ኣልበና በዱንያ ላይ የቆዩት ኣርባ ሁለት አመታት ብቻ ነው ። ስንቱ ነው ኣርባ ኣመት ኖሮ ትዝታው የቅጽበት ቆይታ ያህል የመነመነው? ያም ኣለ ይህ የታላቁ ሸይኽ ሓሰን ኣል በና የስብዕና ምስል የሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ የትልቅነት መልክን ወልዷል ። ትልቅ ሰው ስጋው ብቻ ሳይኾን መንፈሱም ወራሹን ይወልዳልና ። በሸይኽ ዩሱፍ ኣል ቀርዳዊ የሂወት መልክ ላይ መዋጮ ካላቸው ታላላቆች መሓል ሌላኛው ሸይኽ ሙሓመድ ኣልጘዛሊ ናቸው ። ሸይኽ ሙሓመድ ኣልጘዛሊ የመጀመርያው ኢማም ኣቡ ሓሚድ ኣልጘዛሊ እንዳልኾኑ ልብ ይሏል ። ሸይኽ ሙሐመድ ኣልጘዛሊ በ1917 ተወልደው በ1996 እ.ኣ የኖሩ ታላቅ ግብጻዊ ሊቅ ናቸው ። ሸይኽ ሙሓመድ ኣልጘዛሊ በእስልምና ሓይማኖት ጥናት እና በታላቁ ቅዱስ መጽሓፍ ቁርዓን ላይ የሚሰጧቸው ጥልቅ ትንታኔዎች ይወሳሉ ። ከ94 በላይ ድርሳናት የጻፉ ታላቅ የስብዕና ጌጥ ናቸው ። ሸይኽ ሙሓመድ ኣል ጘዛሊ በሸይኽ ዩሱፍ ኣል ቀርዳዊ ህይወትን የነሸጡ እና ወደስኬት ወሰን ያስጠጉ የኔታዎች እንደኾኑ ይነገራል ። ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ሌሎች ዘመናይ ቅጦ
ችን ከኢስላም መርህ ጋር በማረቅም ይታወሳሉ ። ይኼን መርህ የራዕይ ኣብራካቸውን በሚካፈሉት ሸይኽ ዩሱፍ ኣል ቀርዷዊ በኩል ቀጥሏል ። ያም ኣለ ይኽ የሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ የታዳጊነት የእውቀ
ት ሓሰሳ መንገድ ቀጠለ ። የመጀመርያውን የኢስላማዊ ጥናት እንዳጠናቀቁ ወደታላቁ ኣልኣዝሓር የእውቀት ማዕከል ዘለቁ ። በኣል ኣዝሃር የኢስላም የስነመለኮት ጥናትን በ1953 እንዳጠናቀቁ በኣረቢኛ ቋንቋ እና ስነጽሁፍ ዲፕሎማ ከዛው የኣረብኛ ቋንቋ ጥናት ማዕከል ወሰዱ ። በቁርዓን በሓዲሥ እና በኡሉሙ ዲን ወይም የሃይማኖት ሀሁ ወይም በመሰረታዊ ኢስላም ጥናት ማዕከል የኣስኳላ ምሰናው በረታ ። በዛው ማዕከል በ1960 እ.ኣ በቁርዓናዊ ጥናት የማስተርስ ዲግሪ ተቀበሉ ። በ1962 እ.ኣ የእውቀት ዲካው ወደኳታር ተነጠፈ ። ወደኳታር የኢስላም ሃይማኖት እውቀት ማዕከል . . ። በኳታር የፒኤችዲ ጥናታቸውን በዘካ እና በማህበራዊ ፋይዳው ላይ በጻፉት ወረቀት ኣጠናቀቁ ። በወቅቱ የጥናት ወረቀቱ እጅግ ተደናቂ ኾኖ እንደነበር ኣይዘነጋም ።

በ1977 በኳታር ዩኒቨርሲቲ የሸሪዓ እና የኢስላማዊ ጥናት የትምህርት ክፍል የትምህርት ክፍሉ ሃላፊ ኾነው ተሹመዋል ። ከግብጽ ከወጡ በኋላ በኳታር በርካታ ሸሪዓዊ ተቋማትን በተለያየ ሓላፊነት መርተዋል ። በኣልጄሪያ በሚገኝ የኢስላማዊ ጥናት ማዕከል መሪ ኾነውም ቆይተዋል ። ሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ኣቅላቸውን እጅግ ለእውቀት እና ምርምር ያስገዙ ሊቅ ናቸው ። በ1997 እ.አ በኣውሮጳ የፈትዋ የጥናት እና ምርምር ሕብረት ከምስረታው ጀምሮ ግዙፍ ኣበረክቶ ኣድርገዋል ። ሙስሊሞች ህዳጣን ኾነው በሚኖሩባቸው የኣውሮጳ ሐገራት ኢስላማዊ ፈትዋዎች እና የሸሪዓ ጥናቶች እንዲስፋፉ ከተለፉ ልፋቶች ጀርባ ስማቸው ግዘፍ ነስቶ ቆሟል ። በወቅቱ የኣለም ኣቀፍ የሙስሊም ምሁራን ህብረ
ት በመባል የሚታወቀውን ተቋም መርተዋል ። የሓገራቸውን ምድር ከ1961 እ.አ ጀምሮ እንዳይረግጡ ተከልክለው የኣገራቸውን ኣፈር የረገጡት በ2011 እ.ኣ የኣረብ ኣብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን ነበር ። በወቅ
ቱ በታህሪር ኣደባባይ ተገኝተው ለበርካታ ተሰብሳቢዎች ንግግር ሲያደርጉ ታይተዋል ። ከተለያዩ ንግግ
ሮቻቸው እና ጽሁፎቻቸው ያልረገበ በረከቶች ፈልቀዋል ። ከዚህ መሓል በኣልጀዚራ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለረዥም ጊዜ ሲተላለፍ የቆየው አሸሪኣ ወልሃያት የተባለው የቴሌቭዥን ዝግጅት ይታወሳል ። በተለያዩ የበይነ መረብ ገጾች በኩል ያልበረደ የእውቀት ችረታቸው ኣልተሰሰተም ። ሸይኽ ዶክ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ከ120 የሚልቁ ድርሳናትም ከትበዋል ። ይኼ በኣንድ ሰው ኣቅም ሊቻል የማይታሰበው ምጥቀት በሸይ
ኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ተከውኗል ። እኚህ በዘመን መስክ ላይ የበቀሉ የወይን ሓረግ ከሕይወት ማሳቸው የብርሓን እሸት ይቀጠፋል ። ሸይኽ ዩሱፍ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ በፖለቲካዊ በማህበራዊ እና ሌሎች እሴቶ
ች በኢስላም የመርህ ኣይን በመቃኘት እና በመበየን በዘመኑ ፋና ወጊ ናቸው ። በፖለቲካዊ የእሴት ሚዛናቸው ከተለያዩ ወገኖች ልዩነት ቢኖራቸው ኣለም እጅግ ተጽዕኖዋቸው ከጎላ የኢስላም ሊቃውንት ከግንባር ቀደሞቹ መሓል ስማቸውን ኣድምቆ ጽፎታል ። ሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ከጻፏቸው በርካታ መጽሃፍት መሃል ሃላል ወል ሓራም ፊል ኢስላም ተቀዳሚው ነው ። መጽሀፉ በተለያዩ ቋንቋዎች ለመተ
ርጎም በቅቷል ። በኣማርኛም ጭምር ። በኢስላም ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ውቅር በትዳር በቤተሰብ እና ሌሎች የሸሪዓ ጽንሰ ሓሳቦች ላይ ለመሬት ለሰማይ የከበዱ ብይኖች እና ድርሳናት ከትበዋል ። በሙስ
ሊም ወንድማማቾች እንቅስቃሴ ውስጥም እጅግ የደመቀ ስም ኣላቸው ። ሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ የስጋ ልጆቻቸው ባክነው ኣልቀሩም ። እነሱም በራሳቸው የልህቀት መስክ ላይ እያበቡ ነው ። ኢልሃም ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ እና Abdurehman yusuf alqerdawi ኢልሓም በኣለም ኣቀፍ ደረጃ የተፈቀደች የኒውክለር ሳይንቲስት ስትሆን ኣብዱልረህማን ዩሱፍ ደግሞ በግብጽ እውቅ ገጣሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ኣራማጅ ነው ። ስድስት ያህል የግጥም መድብሎች እንዳሳተምም ይነገራል ። ሸይኽ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ በርካታ የእውቅና እና የክብር ሽልማቶች ተቀብለዋል ። በ1991 the islamic develo
pment bank ወይም Idb በኢስላማዊ የምጣኔ ሓብት ጥናት ላበረከቱት ኣስትዋጽኦ ፣ በ1994 የንጉስ ፋይሰል ኣለምኣቀፍ ሽልማት በኢስላማዊ ጥናት እና ምርምር ዘርፍ በ2000 እ.ኣ በዱባይ ኣለም ኣቀፍ የቁርዓን ሽልማት የኣመቱ ግዙፍ ሙስሊም ስብዕና የተባለ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ። የኳታር ኢስላማዊ ጥናትና ምርምር ማዕከል በስማቸው የነጻ የትምህርት እድል ፕሮግራም መስርቷል ። ለበረካው ኣንድ ሁለት ኣልን እንጂ የእውቅናና የሽልማት ተረካቸወወ ብቻውን ሊያውል ይችላል ።

በሁሉም ማዕዘን የሸይኽ ዶክ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊን የስብዕና ዳራ ብንቃኝ በብዙዎች ዘንድ የሚነገርላ
ቸውንና እንደኣርማና ምልክት የሚታዩበት የሸሪዓንም ኾነ ሌላ ኣለማዊ እውቀት የሚረዱበት እና የሚያስረዱበት ሚዛናዊ ምልከታ ነው ። ካላቸው ጥልቅ የእውቀት የጥናት እና የምርምር ግዘፍ ላይ ኹሉንም የእውቀት እና የሸሪዓ ዳር በሚዛን ለማየት በመጣር በዘመኑ ፋና ወጊ እንደኾኑ ይወጋል ። ይኼንኑ ሚዛናዊነትን እንደኣንድ የእውቀት ዘርፍ ወይም እውቀቶችን እና ነባራዊ ሓቆችን እንደማረቂያ ስልት ከመጠቀም ኣልፈው ይኼንኑ ጉዳዬ ብሎ የሚሰራ ተቋምም መስርተዋል ። የኣለም ዘመናይ የፖለቲካ ውቅር እና እጅግ ዳር የያዙትን ብይኖችን በተጠና የሸሪዓ ብይን ለማረቅ እጅግ ለፍተዋል ። በርግጥ ወሰጢያ ወይም ሚዛናዊነት መሓከለኝነት በመሰረታዊው የኢስላም ስርዓት ውስጥ እጅግ ቦታ የሚሰጠው ጽንሰ ሓሳብ ነው ። ሸይኽ ዶክ. ዩሱፍ ኣል ቀርዷዊ በስርዓተ ጾታ በትምሕርት በኢስላማዊ ምጣኔ ሓብት በህዳጣን መብት በቤተሰብ እና በጥበባት ጉዳይ ላይ ሰጧቸው ብይኖችም ይዘከራሉ ። በኳታር የኢስላማዊ ጥናት እጅግ ግዙፉ ኣሻራ የሳቸው ነው ። በሃማድ ቢን ኸሊፋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተቋቋመው ተቋማቸው በሙስሊሞች መሓከል ገንቢ ውይይቶች እንዲፈጠሩ ፣ እዝነት ፍቅር ሰላም መከባበር እና ሌሎች ኣወንታዊ እሴቶች የሰው ልጅ በሚገነባው ማሕበረሰብ መሐል ህይወት ዘርተው እንዲገኙ የተለጠጡ ትርክቶችን በኣንድ የሚዛን መስክ ላይ እንዲሰፍኑ እና ሌሎች ጉዳዮች ሰፋፊ ጥናት እና ምርምሮች ማድረግ እና መስደረግ እና ሌሎች ሰናይ ራዕዮችን ጉዳዬ ብሎ ይሰራል ። ይኸው ተቋም በተቋቋመበት ዘርፍ እና መሰል ሰናይ ራዕዮች ላይ የእጃቸውን ላልሰሰቱ ስብዕናዎች ሽልማትም ይሰጣል ። ሽልማቱም በታላቁ የዘመን ጌጥ በሸይኽ ዶክ ዩሱፍ ኣል ቀርዷዊ የክብር ስም ይጠራል ። የዚህ ዘርፍ ኣበርክቷቸው ብቻውን ዘመን የማይበቃው የጽድቅ መንገድ ነው ።

ሸይኽ ዶክ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ ግጥሞች ጭምር እንዲጽፉ ይነገራል ። ለዚህ እንደናሙና ኣነል ሙስ
ሊም የተባለውን ህብረ ዝማሬ እንደምሳሌ ልናነሳ እንችላለን ። በተለያዩ የእውቀት ኣሰሳ መንገዶ
ቻቸው የዲግሪውን ቀበሌ ተቃንተውታል ። ታላቁ ሰው በቅርቡ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጠቅተው የነበሩ ቢኾንም በኣጭር ጊዜ ውስጥ ኣገግመዋል ። ዛሬ ዶክ ዩሱፍ ኣልቀርዷዊ የ94 ኣመት የእድሜ ባለበረካ ኾነዋል ። እድሜያቸው በዋዛ ያልባከነ ፣ የረገጡት የህይወት ፈለግ በሙሉ ለምለም እና ጸዓዳ እንደኾነ እስካሁን ሰንብተዋል ። ኣላህ በማያልቀው የጸጋ ችረቱ ኣሁንም ያቆያቸው ። ለእኛም ያልባከነ የእድሜ በረከቱን እንታደል ። እድሜያቸውን በበረካ ድሪ እንዳስጌጠው ኻቲማቸው ያማረ ይሁን ! እኛንም በትልቆቹ የብርሃን ፈለግ ይልቀቀን ። ኣማን ሁኑ !

የ ካሊድ መንገድ

በሁዳ ኬ.

ከካሊድ ጋር የተዋወቅነው ትምህርት ቤት ነው፡፡ ፈታ ያለ ልጅ ነው፡፡ ምንም ነገር ለማድረግ ከቤተሰቡም ሆነ ከሌሎች ሰዎች አይደባበቅም፡፡ ይቅማል፣ ያጨሳል- ማለቴ ሺሻም ይሞክራል፡፡ እውነቱን ለመናገር እኔና ሌሎች በቡድን የምናስብና የምንንቀሳቀስ የካሊድ ጓደኞች ጫትም ሆነ ሺሻ የለመድነው እሱን ታከን ነው ብል ለእውነት ሩብ ጉዳይ ሀቅ እንዳወራሁ ነው የሚሰማኝ፡፡

ምላሱ ላይ የተነቃሳት የምትመስለን የካሊድ እናት የሁላችንም እናት እንደዛ በሆኑልን ብለን እስክንመኝ ትመቸናለች፡፡ ባጠቃላይ የካሊድ አኗኗር ህልማችን ነው፡፡ እርግጥ ነው ከሱ ጋር በነበረን ትስስር ከዲናችን እየራቅን መምጣታችን ሳይታወቀን ነጉደን ነበር፡፡ እስማኤል እስኪቀላቀለን፡፡ ባጭሩ እስማኤል ሙሴያችን ሆኖ ታደገንና የተበላሸው ሂወታችን መስመር እየያዘ ወደ አላህ እየተቃረብን በኢባዳ እየበረታን‹ ከሱስ እየተፋታን መጣን፡፡

የዚህን ጊዜ በካሊድና በእናቱ መሃከል ያለው ክፍተት በደንብ ገባን፡፡ ካሊድ በዙርያው ጓደኛ እንጂ ቤተሰብ እንደሌለው ተረዳን፡፡ እንዴት ማለት ጥሩ… እንዴት በሉ… የካሊድ እናት ካሊድን ስትወልድ ልጅ ወልዶ ለማሰደግም ሆነ ከስሜት ከፍ ብሎ ስለማሰብ ደንታ አልነበራትም፡፡

ይህን ስል አዝናለሁ ነገር ግን የሆነው እንደዛ ነው… አለማወቅ ሊሆንምኮ ይችላል፡፡ ቢሆንም ካሊድ ከልጅነቱ ጀምሮ ያደገው ፐ!  ዘመናዊ እናትስ እንደሱ እየተባለ በሌሎች እየተቀናበት ቢሆንም… በዘመናዊነት ስር የተደበቀው የናቱን የናትነት ሚና መጉደል ማንም ሳያስተውልለት ክፍተቱን እያሰፋ ነው ያደገው፡፡ እናቱ ከልጇ ፊት ልትደብቀው ያልቻለችው አላህን የሚያስቆጣ ባህሪና ተግባራቶቿ በሱ የልጅነት ሚዛን ልክ ናቸው ተብለው ሲሰፈሩ ነው ያደገው፡፡ 

ወላጆቹ ጥፋታቸውን፣ የወላጅነት ሚናቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት የሚመጣውን ቀውስ ለልጃቸው የፈለገውን ነገር እንዲያደርግ በመፍቀድ ነው ያካካሱት፡፡ በህይወቱ ክልከላ የለም፡፡ ህግ የለም፡፡ ስርዓት የለም፡፡ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንደሚችል ነው የሚያውቀው፡፡ መቃም የፈለገ ቀን እናቱ ጋር ፈርሾ፣ መውጣት የፈለገ ቀን ሴት ጓደኞቹን በናቱ ስልክ ጠርቶ ማማዬ ዛሬ አድራለሁ አትጠብቂኝ ብሎ ራስህን ጠብቅ ተብሎ ነው የኖረው፡፡ ከሙስሊም ቤተሰብ ቢወለድም የእስልምና ድንበር የት ድረስ እንደሆነ ሳይነገረው፣ ከዚህች ሀገር ተሸግሮ ሌላ ህይወት እንደሚጠብቀው ሳያውቅ ነው የኖረው፡፡ 

ከኛ ጋር የገጠመ ሰሞን ለሰላት የምናሳየው መጠዳደፍ ይገርመው ነበር፡፡ በዚህ እድሜያችን ለመስገድ ማሰባችን ራሱ ይደንቀዋል፡፡ ለሱ የሚገባው ሰላት የትልልቅ ሰዎች ጉዳይ እንደሆነ ነው፡፡ ዲን ማለት ለሱ ቤታቸው ተፈርሾ ዱኣ ሲደረግ አሚን፣ አሚን በሚባለው ኢባዳ የተወሰነ ነው፡፡ ሙስሊም መሆኑን ቢያውቅም እስልምና እንደብሄሩ ወይም ጾታው የተጫነበት አንድ ማንነት እንጂ ህግና ስርዓት ያለው የህይወት መመርያ መሆኑን አያውቅም፡፡ 

ቁርዓን መቅራት ቢችልም ወደ አላህ በመከጀል ሚቃረቡበት መሳርያ መሆኑን አይገነዘብም፡፡ ባጠቃላይ ለሱ አለም እናቱ ባሰመረችለት መስመር ውስጥ የሚርመሰመስ ዑደት እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡