ስለ እኛ

ሚንበር ቲቪ

ሚንበር ቲቪ ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወደ ህዝብ ከሚያደርሳቸው ሥራዎቹ አንዱ ሲሆን አየር ላይ በዋለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቅቡለነትን በማትረፍ በዘርፉ ከሚጠቀሱ ጣቢያዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ የቴሌቪዥን ቻናል ነው፡፡ 

በአሁኑ ሰዓት የሚንበር ቲቪ ስርጭት በመላው ዓለም በኢትዮ-ሳት በፍሪኩዌንሲ:- 11545፣ ሲምቦልሬት:- 30000 እንዲሁም ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡

ስለ ህጋዊነት

ተቋማችን ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በንግድ ፈቃድ ቁጥር ar/aa/14/640/4009124/2007 በንግድ ምዝገባ ቁጥር ar/aa/2/0003784/2007 እና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0043170734 ተመዝግቦ በተንቀሳቃሽ ፊልም፣ ራዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና ሌሎች የማዝናናት አገልግሎት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ራዕይ

ጥራት እና ጥበባዊ ፈጠራን መለያቸው ያደረጉ ሚዲያ ውጤቶችን አምርቶ ለህዝብ በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ ሁለንተናዊ ከፍታን የሚያመጣ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሆኖ መገኘት!

ተልዕኮ

በፈጠራ የታገዘና በጥራቱ የላቀ አገልግሎት በመስጠት የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት!

ዓላማ

  • የመገናኛ ብዙኃን ውጤቶችን በመጠቀም የኢስላምን ብሎም የሃገራችን ውብ ገጽታ ለዓለም ማስተዋወቅ!
  • ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥን ለማዳበር በመስኩ የበቁ ሙያተኞችን ማፍራት!
  • የማህበረሰባችንን እሴቶችና መልካም ባህሎች ጠብቆ ለማቆየት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የጎላ ተሳትፎ ማድረግ! – የደንበኞቻችን ፍላጎት ያማከለ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠትና ጤናማ የሥራ ግንኑነት በማስፈን ትርፋማ ሆኖ መገኘት! – ስለ እስልምና ለሌላው ማኅበረሰብ በጥበብ በማስተማር፤ ልዩነቶችን ባከበረ መልኩ ማቀራረብ!

Submit your video

Would you like to share your creativity with the world? Submit your video by clicking on the button below.

Submit your video